ማስታወቂያ
የተለቀቀበት ቀን: 02/04/2017 ዓ.ም
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በንግድ ሕግ አንቀጽ 366፣ 367፣ 370፣ 371፣ እና 372 መሰረት ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ራስ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የባለአክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡ ስለዚህ ባለአክስዮኖች በተጠቀሰው ቀን፣ ሰአትና ቦታ በመገኘት ተሳታፊ እንድትሆኑ የተቋሙ የዳሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዳይሬክተሮች ቦርድ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 251-11 124 6822 ወይም 251-929-010-203
አገልግሎቶቻችን
የብድር አገልግሎታችን በልዩ ሁኔታ የሥራ ፈጣሪዎችን፤ ጀማሪ የንግድ ተቋማት እና ሌሎች የብድር አገልግሎት ፈላጊ ደንበኞቻችንን ለመደገፍ እና ትርፋማ ለማድረግ ታስበው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ውስን መስፈርቶችን በማሟላት ብቻ ቀላል እና ቀልጣፋ የብድር አገልግሎታችን የምናስተናግድዎ ይሆናል። የደንበኞቻችንን ፍላጎቶች ለማሟላት ለቀልጣፋ አሠራር እና ተደራሽነት ቅድሚያ መስጠታችን የብድር ሂደቱን ለማቀላጠፍ ይረዳል።
ዝርዝር ይመልከቱየቁጠባ አገልግሎታችን ለደንበኞቻችን ተወዳዳሪ እና አስደሳች የወለድ ተመኖችን የምናቀርብበት አገልግሎታችን ነው፡፡ ደንበኞቻችን በማንኛውም ሰዓት ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ቀላል፣ ምቹ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ባሉበት ቦታ የቁጠባ ተቀማጭ መሰብሰብን ጨምሮ ማንኛውንም የቁጠባ አገልግሎት የምንሰጥ ይሆናል። ይህም የደንበኞቻችንን የቁጠባ እድገት የሚያረጋግጥ፣ ጉልበት ቆጣቢ እና ቀልጣፋ አሠራር ነው።
ዝርዝር ይመልከቱየፋይናንስ የማማከር አገልግሎታችን ደንበኞቻችንን ኢንቨስት በሚያደርጉበት ማንኛውም ቢዝነስ ጠንካራ አቋም እንዲኖራቸው፣ የበጀት አስተዳደር፣ በእቅድ የተመራ የቢዝነስ አሠራር እና የፋይናንስ ስትራቴጂ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ግንዛቤ እንዲያገኙ የሚረዳቸው አገልግሎታችን ነው።
ዝርዝር ይመልከቱመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ የደንበኞቹን የፋይናንስ እውቀት እና የሥራ ፈጠራ ችሎታቸውን እንዲያሳድጉ የታለሙ የሥልጠናዎችን ይሰጣል። በዚህም እንደ በጀት ዝግጅት፣ የብድር አስተዳደር፣ የንግድ ልማት እና የኢንቨስትመንት ስትራቴጂዎች የመሳሰሉ ጠቃሚ ርዕሶችን ይካትታሉ።
ዝርዝር ይመልከቱደንበኞች ለምን እኛን ይመርጣሉ!
ደንበኞቻችን የብድር አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተቋማችን ሲመጡ በፍጥነት እንዲደርስላቸው ቀልጣፋ የሆነ መስተንግዶ ከተቋማችን ያገኛሉ።
የብድር አገልግሎታችን ለብድር መስፈርት ብቁ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሁሉ አለምንም ልዩነት የምንሰጥ በመሆኑ የምናቀርበውን የፋይናንስ ድጋፍ ለማህበረሰባችን ተደራሽ እና አካታች ያደርገዋል።
አዲስ ቢዝነስ ለጀመሩ ግለሰቦች ልዩ የብድር አገልግሎት እንሰጣለን፤ ይህ አገልግሎት ሥራ ፈጣሪዎችን በማበረታታት በሐሳብ ደረጃ የያዙትን የሥራ ክህሎታቸውን ወደ ተግበር ለመቀየር እንዲችሉ የፋይናንስ ችግርን በመቅረፍ አይነተኛ ሚናን ይጫወታል። በአጠቃላይ ደንበኞቻችን በተሰማሩበት ቢዝነስ ውጤታማ እንዲሆኑ ዘላቂ ድጋፍ እና ክትትል ይደረግላቸዋል።
ዜና
የመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የተቋሙ ዳሬይክተሮች፣ ጥሪ የተደረገላችው እንግዶች እና የተቋሙ ሠራተኞች በተገኙበት ዛሬ መጋቢት 13/ 2017 ዓ.ም ሦስተኛ ቅርንጫፉን በመክፈት በይፋ ሥራ ጀምሯል፡፡
ዝርዝር ይመልከቱበቅርቡ ወደ ፋይናንስ ሴክተሩ የተቀላቀለው መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. አንደኛ መደበኛ እና አንደኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. በራስ ዓምባ ሆቴል አካሒዷል፡፡
ዝርዝር ይመልከቱመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የመጀመሪያ የሆነውን ቅድስተ ማርያም ቅርንጫፍ የተቋሙ የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላችው እንግዶች እና የተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት ሠራተኞች በተገኙበት ዛሬ ሐምሌ 29/ 2016 ዓ.ም በመክፈት በይፋ ሥራ ጀመረ።
ዝርዝር ይመልከቱመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ሥራ በመጀመር የፋይናንስ ዘርፉን ተቀላቀለ። ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንከ ፈቃድ በማግኘት በዛሬው ዕለት ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ ሥራ መጀመሩን አብስሯል።
ዝርዝር ይመልከቱመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ሁለተኛውን ቅርንጫፍ የተቋሙ ሥራ አመራር አባላት ፣ ጥሪ የተደረገላችው እንግዶች እና የተቋሙ ሠራተኞች በተገኙበት ዛሬ ነሐሴ 25/ 2016 ዓ.ም በመክፈት በይፋ ሥራ ጀመረ።
ዝርዝር ይመልከቱአጋር ድርጅቶቻችን