መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ በአዲስ አበባ ዋና መሥሪያ ቤት እና ሁለት ቅርንጫፎች ያለው ሲሆን በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ቅርንጫፎች የሚያስፋፋ ይሆናል። የቅርንጫፎች መክፈቻና የአገልግሎት ማስፋፊያ ይበልጥ ስልታዊ እና ዲሲፕሊን ያለው የንግድ ዳሰሳ እና ደረጃ በደረጃ የሚከናወን የአደጋ ግምገማ ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
ተልዕኮ
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ቴክኖሎጂን በመጠቀም እና ከፍተኛ ብቃት፣ የሥራ ተነሳሽነት፣ ብቃት እና ሥነ ምግባር ያለው የሰው ኃይል በማሰማራት አዳዲስ የፋይናንስ እና ገንዘብ ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶችን በማቅረብ ለደንበኞቻችን እሴት መፍጠር ነው ።
ርዕይ
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በሁሉም አገልግሎቶቹ በዲጂታል ትክኖሎጂ በመታገዝ ግንባር ቀደም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም መሆን
ግብ
በፈጠራ እና በዘላቂ አገልግሎት ለተቸገሩ ደንበኞች የብድር፣ ቁጠባ እና የገንዘብ መፍትሔዎችን መስጠት
ለደንበኞቻችን የኢንቨስትመንት ገቢን በማረጋገጥ በዕቅድ የተመራ የንግድ ክህሎትን በማዳበር እና አገልግሎት በመስጠት በገጠርና በከተማ የሥራ ፈጠራን ማበረታታት።
ድህነትን ለመቅረፍ በቀላሉ ተደራሽ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ዘላቂነት ያለው የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት የኑሮ ደረጃን ማሻሻል፣ የተሻለ ንብረት መገንባት እና የበለጠ ጠንካራ የሲቪል ማኅበረሰብ መፍጠር፣
ዋና እሴት
የመባዕ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ እሴቶች፡
ፈጠራ
ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው የደንበኛ አገልግሎቶች
ብቃት እና ውጤታማነት
ፍትሐዊነት፣ ግልጽነት እና ከፍተኛ የሥነ ምግባር ደረጃዎች
ለፈጠራ እና ለቡድን ሥራ ታማኝ መሆን እና አክብሮት መስጠት