የሴቶች ቁጠባ አገልግሎታችን ሴቶች የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ እና እራስ አገዝ የፋይናንስ አቋም እንዲኖራቸው የሚያበረታታ ሲሆን ከፍተኛ የወለድ ተመን የሚታሰብለት ይሆናል። ይህ ልዩ አካውንት የተነደፈው በተቀማጭ ገንዘብ ላይ የላቀ ተመላሽ በማድረግ ሴቶችን ለመደገፍ እና ለማበረታታት ነው።
ይህ አገልግሎት የፋይናንስ ደህንነታቸውን ከማጎልበት ባለፈ ለግል እና ለሙያ እድገት ካፒታል እንዲያገኙ ምቹ እና ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ አቅም እና ነፃነትን ያጎናጽፋል።