የጊዜ ገደብ ቁጠባ አገልግሎት ደንበኛው አስቀድሞ የተስማማው የገንዘብ መጠን ለተወሰነ ጊዜ በጊዜ ገደብ የሚቀመጥበት እና ከፍተኛ የወለድ ተመን የሚታሰብለት የቁጠባ አማራጭ ሲሆን ለተቀማጭ ገንዘብ የሚታሰብለት የወለድ ተመን መጠን እንደአስፈላጊነቱ ለድርድር የሚቀርብ ነው። ይህ ዓይነቱ ተቀማጭ ገንዘብ ከሌሎች የቁጠባ አማራጮች ጋር ሲነጻጸር ከፍ ያለ የወለድ ተመን የሚታሰብለት ይሆናል።
በተጨማሪም፣ የጊዜ ገደብ ተቀማጮች የፋይናንስ ፍላጎቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ ከተመቻቹ የብድር ውሎች እና የተፋጠነ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን በማረጋገጥ ቅድሚያ የብድር አገልግሎት ያገኛሉ። ይህ እየተሻሻለ ለሚመጣ የቁጠባ እድገት እና ፈጣን የብድር አግልግሎትን በማግኘት ባለው ጥቅም የእኛን የቋሚ ጊዜ ተቀማጭ ገንዘብ የፋይናንስ ስልታቸውን ለማሻሻል ለሚፈልጉ ሰዎች ማራኪ ምርጫ ያደርገዋል።