ይህ ለተወሰነ ዓላማ የተነደፈ የቁጠባ ዓይነት ነው፣ ከእነዚህም ውስጥ ለትምህርት፣ ለህክምና፣ ለሰርግ እና ቋሚ ንብረቶችን ለመግዛት ለምሳሌ መኖሪያ ቤት እና መሰል ንብረቶች ገዢ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያገለግል ነው። በዚህ ሂሳብ ውስጥ የተቀመጠው ገንዘብ ለተጠቀሰው ዓላማ ብቻ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞችን እና ወጣት ጎልማሶችን አመቺ በሆኑ የፋይናንስ ምርጫዎች ለማገልገል፣ ጤናማ የፋይናንስ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ፣ ንብረታቸውን እንዲያሳድጉ እና በራሳቸው የወደፊት ጊዜ ላይ ቀድመው ኢንቨስት ለማድረግ እንዲያስቡ የልዩ ዓላማ የቁጠባ አገልግሎትን ይሰጣል።