ይህ የብድር ዓይነት በዋናነት በከተማ እና በገጠር ያለውን የንግድ ሥራ እና በጅምር ወይም በመስፋፋት ላይ ላሉ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ታስበው የተዘጋጀ ነው።
አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ብድር ደንበኞች የተፈጥሮ ሰው እና/ወይም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች (ማኅበራት፣ አክሲዮን ኩባንያዎች፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ የኅብረት ሥራ፣ አጋርነት እና ሌላ ድርጅት) ሊሆኑ ይገባል።
የድርጅቱ የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ
የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
ታማኝነት፣ መልካም ስነ ምግባር እና የብድር ብቁነት አስፈላጊ ናቸው፡፡