የአረጋውያን ቁጠባ ሂሳብ በተለይ እድሜያቸው 55 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ግለሰቦች የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህም ለአረጋውያን ፍላጎቶች የተዘጋጀ አስተማማኝ እና ጠቃሚ የቁጠባ አማራጭ ነው። ይህ የቁጠባ አይነት ከፍተኛ የወለድ ተመን ወይም የጡረታ ቁጠባቸውን የሚደግፉ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችን የሚያገኙበት የአረጋውያንን የፋይናንስ አቅም የሚያሳድግ የቁጠባ አይነት ነው፡፡ ይህ አገልግሎታችን ምቹ እና አረጋውያን በቀላሉ ገንዘባቸው ወጪ የሚያደርጉበት ቀልጣፋ አገልግሎትን የሚሰጥ ይሆናል።
በተጨማሪም የአረጋውያን ቁጠባ ሂሳብ በጡረታ ጊዜ ቁጠባን በብቃት ለማስተዳደር እና የፋይናንስ አቅምን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት እና የፋይናንስ እቅድ ምክር ይሰጣል። ይህ አገልግሎት የአረጋውያን የገንዘብ አቅም ለማሳደግ እና የአእምሮ ሰላምን ለመስጠት፣ በጡረታ ዓመታቸው ልዩ የገንዘብ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት እና የሕይወት ዋስትናቸውን ለማሳደግ ያለመ ነው።