የሙዳይ /የሣጥን ቁጠባ አገልግሎታችን ለመቆጠብ ቁርጠኛ ለሆኑ እና ቁጠባቸውን በቀላሉ ባሉበት ቦታ ማስቀመጥ ለሚመርጡ ግለሰቦች የተዘጋጀ ነው። ደንበኞች በሥራ ቦታቸው ወይም በቤታቸው የሚጠቀሙበት ደህንነቱ የተጠበቀ ሳጥን እናቀርባለን። ይህ የቁጠባ አማራጭ ቀላል እና ምቹ ተንቀሳቃሽ የቁጠባ ሂሳብ የማንቀሳቀስ እድል ይኖረዋል፣ እንዲሁም ከከፍተኛ የወለድ ተመን ጋር ተዳምሮ የፋይናንስ እቅምን ከፍ ለማድረግ ይረዳል።
በተጨማሪም የሙዳይ/የሳጥን ቆጣቢዎች የብድር ፍላጎት ሲኖራቸው ከተመቻቹ የብድር ውሎች እና ቀልጣፋ አገልግሎታችን ተጠቃሚ መሆናቸውን በማረጋገጥ ቅድሚያ ብድር ያገኛሉ። ይህ የተቀናጀ አካሄድ የቁጠባ እና የብድር ሂደቱን ይደግፋል፣ በዲሲፕሊን የተደገፈ የቁጠባ ልማድን በማስተዋወቅ ምቹ የፋይናንስ አገልግሎትን ይሰጣል።